Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የሚኒስትሮች ምክር ቤት 26ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

December 20, 2023
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ታህሳስ 10፤ 2016- የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 26ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

26ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሣ የሚከፈልበትን እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን በቀረበው ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡

መንግስት ለሕዝብ ጥቅም በሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች ሲባል የመሬት ይዞታ እንዲለቁ ለሚደረጉ ባለይዞታዎች ተገቢና ተመጣጣኝ ምትክ ይዞታ፣ ካሣ መስጠትና ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል ግምት ውስጥ መግባት የሚገባቸውን መሠረታዊ መርሆዎች ለመደንገግ፣ ካሣን የመተመን፣ የመክፈል እንዲሁም ተነሺዎችን መልሶ የማቋቋም ሥልጣንና ኃላፊነት የተጣለባቸውን አካላት እና ግዴታዎቻቸውን በግልጽ መድረግ በማስፈለጉ በስራ ላይ ያለውን አዋጅ ቁጥር 1161/2011 የሚያሻሽል ረቂቅ አዋጅ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

2. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየዉ የሜዳይ፣ ኒሻን እና ሽልማት ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ በልዩ ልዩ ዘርፎች የላቀ ተግባር ለፈጸሙ ዜጎች እና ግለሰቦች እዉቅና መስጠት በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ለሀገር ለሚያበረክቱት የላቀ አስተዋጽኦ ኢትዮጵያ ባለዉለታ አድርጋ እንደምታከብራቸዉ እውቅና የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ ሌሎችም የእነርሱን አርአያነት እንዲከተሉ የሚያበረታታ፣ የስራ ፈጠራ እንዲስፋፋ፣ ሁለንተናዊ እና ቀጣይነት ያለዉ ብልጽግና እንዲረጋገጥ ፋይዳው የላቀ በመሆኑ በኢፌ.ዴ.ሪ ሕገ-መንግሥት የተደነገገውን የሜዳይ፣ የኒሻን እና የሽልማት አሰጣጥ ስርዓት መተግበር የሚያስችል፣ ለአተገባበሩም ህጋዊ ሥርዓት የሚዘረጋ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል እንዲጸድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

3. በተጨማሪም ምክር ቤቱ የሕዝብ በዓላትን፣ የዕረፍት ቀናትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቷል፡፡ የሕዝብ በዓላት እና የእረፍት ቀናት ለዜጎች ሥነ-ምግባርና ስነ-ልቦና ግንባታ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦዋችው ከፍተኛ በመሆኑ ሕጋዊ እውቅና መስጠት እና በብሔራዊ ደረጃ እንዲከበሩ ማድረግ የሚገባ በመሆኑ፤ ኃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ታሪካዊ ሥርዓታቸውን ጠብቀው ሊከበሩ የሚገባ በመሆኑ፤ የዜጎችን የእርስ በእርስ መልካም ግንኙነትና መተሳሰብ የሚያጎለብቱ እንዲሆኑ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል እንዲጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል::

4. በመጨረሻ ምክር ቤቱ የተወያየው በአምራች ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ነው፡፡ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት እና መዋቅራዊ ሽግግር መሳለጥ የላቀ ሚናውን እንዲወጣ፤ ለውጪ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እና ለዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጠራ መደላድል የሚሆን የፖሊሲ ማእቀፍ ሚያስፈልግ በመሆኑ፤ የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ ለማሳደግና ለማበረታታት፣ የኢንዱስትሪዎች መስፋፋት በአካባቢና በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ክብካቤ መርሆዎቻችን ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፣ ከሌሎች ዘርፎች ጋር ያለውን ትስስርና ቅንጅት ለማሳደግ የሚያስችል ረቂቅ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/

Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

የኮሎራዶ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትራምፕን ከገዛቲቱ የምርጫ ውድድር ሰረዘ

Next Post

ታሪክ ሲጨለፍ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ታሪክ ሲጨለፍ

ታሪክ ሲጨለፍ

ባህርዳር እና የቻይናዋ ዱጃንየ ከተሞች የእህትማማችነት ስምምነትን ተፈራረሙ

ባህርዳር እና የቻይናዋ ዱጃንየ ከተሞች የእህትማማችነት ስምምነትን ተፈራረሙ

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የሚሰጡ አገለግሎቶች የሃገር ገጽታን የሚገነቡ እንዲሆን ተጠየቀ

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የሚሰጡ አገለግሎቶች የሃገር ገጽታን የሚገነቡ እንዲሆን ተጠየቀ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?