አዲስ አበባ | ታህሳስ 09፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባዔ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል፡፡


ምክር ቤቱ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እንዲሾሙ የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡
ምክር ቤቱ በሌላ በኩል አቶ ጌትነት ታደሰን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾሟል፡፡አቶ ጌትነት ታደሰ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው አቶ መሳፍንት ተፈራን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አድርጎ ሾሟል፡፡ ምክር ቤቱ በ9ኛ መደበኛ ስብሰባው የ8ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔንም አጽድቋል፡፡
በሰላማዊት ወንድወሰን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












