አዲስ አበባ | ታህሳስ 05 ፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የአሜሪካ ባለስልጣናት እስራኤል ያልተቋረጠ የአየርና የምድር ውጊያዋን በጋዛ ማቆም እንዳለባት አሳስበዋል፡፡

ባለስልጣናቱ ትላንት ሀሙስ በተሰበሰቡበት ወቅት በሳምንት ውስጥ ጦርነቱን በማቆም ሀማስ በሚገኝበት ቦታ ብቻ ዉጊያዋን ማድረግ አለባት ብለዋል ፡፡
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ከእስራኤል ባለስልጣናት ጋር ስለጦርነቱ ሁኔታ መምከራቸውንም አስታውቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ጆባይደን እስራኤል በሶስት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጦርነቱን መጨረስ አለባት ማለታቸውን ከነጩ ቤተ መንግስት መረጃ መገኘቱን ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook –https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv