አዲስ አበባ |ታህሳስ 04፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ዲሜንሺያ የተባለው የአዕምሮ ህመም የማስታወስ እና የተግባቦት ፣ ውሳኔ መስጠት ላይ መቸገርን እና በብዥታ የተሞላ አስተሳሰብን ያካተተ ነው፡፡ በብዛትም እድሜያቸው 65 እና ከዛ በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ የሚስተዋል ሲሆን፤ በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ስሜታችውን መቆጣጠር አይችሉም፡፡ በተለይ ደግሞ ከንዴት ጋር በተገናኘ የተለያዩ የዲሜንሺያ ዓይነቶች ቢኖሩም ዋናው ግን አልዛይመር ነው፡፡ ይህ በሽታ በሀገራችን ላይ በቁጥር ይህ ነው ብለን ባናስቀምጠውም በአሜሪካ ሀገር በተሰራ የዳሰሳ ጥናት ግን እስክ 5 ሚሊዮን የሚደርሱ ተጠቂዎቸ አሉ፡፡

ዲሜንሺያ የተባለው ህመም ምልክቶች ተብለው ከተገለፁት መካከል፤ ከላይ እንደጠቀስነው፤ አንድ ሰው የአስተሳሰብ እና የማስታወስ ችግር አጋጥሞት ይህ ደግሞ እለት ተዕለት የህይወቱ ክንውኖች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያመጣበት ከሆነ (ለምሳሌ ቤት ማፅዳት፣ ምግብ ማብሰል፣ መድኃኒት መውሰድ፣ መብላት፣ መሰረታዊ የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀም)፤ በህክምና ባለሙያ የሚሰጡ መመዘኛዎች የማስታወስ ችግር እንዳለበት የሚገልፁ ከሆነ፣ ወደ ሆነ ቦታ ለመሄድ አስቦ የሚሄድበትን ወይም መመለሻውን መርሳት፣ ስለ ሰዎች ስሜት አለመጨናነቅ እና ገንዘብ በትክክል መጠቅም ሳይችል ሲቀር፣ እንደ ምልክት የሚያዝ ነገር ነው፡፡
የተለያዩ ዓይነት ዲሜንሺያ እንዳሉ ባለሙያዎች ይነግሩናል፤ ከእነዚህም መካከል፡-
ሀ. አልዛይመር (Alzheimer’s)

እድሜያቸው በገፉ ሰዎች ላይ በብዛት የሚስተዋለው የዲሜንሺያ ዓይነት ነው፡፡ መንስዔዎቹም በእድሜ ምክንያት አንጎል ላይ የሚከሰቱ ፣ አካባቢያዊ ለውጦች፣ ጄኔቲካል ለውጥ እና ጤናማ ያልሆነ የህይወት ዘዬ ይገኙበታል፡፡
ለ. ፍሮንትቴምፖራል ዲሜንሺያ(Frontotemporal dementia) ፡- ይህ ደግሞ በጣም ያልተለመደ ዓይነት ዲሜንሺያ ሲሆን ከ60 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች ላይ የሚታይ ነው፡፡

ሐ. ሌዊ ቦዲ ዲሜንሺያ(Lewy body dementia) ፡- ሐ. ሌዊ ቦዲ ዲሜንሺያ(Lewy body dementia) ፡- ያልተለመዱ የፕሮቲን (አልፋ ሲኑክሌይን) ወይም ሌዊ ቦዲ የተባሉ ዓይነቶች በሰውነታችን ውስጥ ከመጠን በላይ ሲጠራቀም፡፡

መ. ቫስኩላር ዲሜንሺያ(Vascular dementia)፡- በአንጎል ውስጥ ያሉ የደም ቧንቧዎች ላይ በሚኖር ተፅዕኖ የደም እና የኦክስጅን ፍሰት መቆራረጥ አማካኝነት የሚከሰት ነው፡፡

ሠ. ድብልቅ ዲሜንሺያ፡- ከላይ ከተጠቀሱት ዓይነቶች ሁለቱ እና ከሁለቱ በላይ ሲከሰት የሚያጋጥም ነው፡፡

ዲሜንሺያን ያመጣሉ ተብለው ከሚጠቀሱ ምክንያቶች መካከል በዋናነት የሚነሱት የታይሮድ ችግር፣ የቫይታሚን እጥረት፣ የአንዳንድ መድኃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት፣ ድባቴ፣ ጭንቀት፣ጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ፣ የፓርኪንሰን በሽታ እና ሌሎችም የጤና ችግሮች ይገኙበታል፡፡
ዲሜንሺያን ለመከላከል ባለሙያዎች የተለያዩ ጥንቃቄዎችን እንድንወስድ ይመክራሉ ከእነዚህም መካከል በዋናነት የሚገኘው የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ማድረግ ከእነዚህም ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ጤናማ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ በቂ ውኃ፣ ፍራፍሬ፣ የአትክልት እና ጥራጥሬን በማዘውተር የስኳር እና የስብ መጠናቸው ከፍ ያሉ ምግቦችን መቀነስ ይመከራል፤ ከዚህ በተጨማሪም ማህበራዊ ተሳትፎን ከቤተሰብ እና ጓደኛ ጋር መጨመር በዲሜንሺያ የመያዝ እድልን ዝቅ ያደርገዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












