አዲስ አበባ |ታህሳስ 05፤ 2016| NBC ETHIOPIA – በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘውን የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች እየጎበኙ ነው።


በመዲናዋ የትላንትን ታሪክ ለዛሬው ትውልድ የሚተርከው የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ከአራት ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት እየተገነባ ይገኛል ተብሏል።
ይህ ፕሮጀክት የአፍሪካዊያንን የድል ተምሳሌት የሆነውን የአድዋ ታሪክ ለዛሬው ትውልድ የሚያወሳ ሙዚዬም መሆኑም ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ጥላሁን ወርቁ ከተማ አስተዳደሩ ሰው ተኮር የሆኑ በርካታ ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት እየገነባ መሆኑን አክለዋል።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












