አዲስ አበባ | ታህሳስ 01፤ 2016| NBC ETHIOPIA- በ16ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ መርሐ ግብር ትላንት፣ ግራናዳን ከአትሌቲክ ቢልባኦ ያገናኘው ጨዋታ በ17ኛው ደቂቃ መቋረጡ ይታወሳል።

ላለፉት 16 ዓመታት የዓመት ትኬት ሲገዛ ነበር የተባለ አንድ የባለሜዳው ቡድን ደጋፊ ስታዲዮም ውስጥ በልብ ድካም ህይወቱ ካለፈ በኋላ ጨዋታው ለ60 ደቂቃዎች ገደማ ተቋርጦ ለዛሬ ተላልፎ ነበር። ቢልባኦ በኢናኪ ዊሊያምስ ጎል አንድ ለምንም እየመራ ነበር።
ላሊጋው እንዳስታወቀው፣ ጨዋታው ዉጤቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ዛሬ ምሽት 5፡00 ከተቋረጠበት ደቂቃ ይቀጥላል። ደጋፊዎች በትላንቱ ትኬት እንዲገቡ ተፈቅዶላቸዋል።
የቢልባኦ ግብ ጠባቂ ኡናይ ሲሞን፣ የተፈጠረውን ነገር ለዳኞች ለማሳወቅ ላደረገው ከፍተኛ ጥረት ከግራናዳ ደጋፊዎች ዘንድ ምስጋናና ጭብጨባ ተችሮታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv