አዲስ አበባ | ህዳር 28፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የቶትንሀም አሰልጣኝ አንጅ ፖስትኮግሉ፣ ቡድናቸው ማራኪ እግር ኳስን ከመጫወት ባሻገር ተጋጣሚዎቹን የሚረታ መሆን አለበት ብለዋል።

ከ10ኛ ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር በኋላ አንድም ጨዋታ በድል ለመወጣት የተሳናቸው አወስትራሊያዊው አሰልጣኝ፣ ስብስባቸው የትክክለኛ ዉሳኔ ችግር እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ስፐርስ ትላንት ምሽት በሜዳው በዴቪድ ሞይስ ዌስትሀም የደረሰበትን የ2-1 ሽንፈት ጨምሮ ነጥብ በጣለባቸው ያለፉ አምስት ጨዋታዎች በሁሉም ቀድሞ ጎል አስቆጣሪ ነበር።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ ፍጹም የጨዋታ የበላይነት ወስዶ እንኳ ድል ማድረግ እየተሳነው ነው።
የጄምስ ማዲሰን፣ ሚኪ ቫን ደ ቬን፣ ሪቻርልሰን፣ ኢቫን ፐሪሲችና ፓፕ ሳር ከሜዳ መራቅ ለውጤት መጥፋቱ ከሚሰጡ ምክንያቶች መካከል ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv












