አዲስ አበባ | ታህሳስ 02፤ 2016| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ማሽነሪዎችን በሊዝ ፋይናንስ ለተሰማሩ ደንበኞቹ አስረከበ።




ባንኩ ማሽኖቹን ያስረከበው በግብርና እና የማዕድን ዘርፍ ለተሰማሩ የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ ነው። ልማት ባንክ 20 በመቶ ሲቆጥቡ ለነበሩ አልሚዎች ነው ማሽነሪዎቹን ያስረከበው።
በወረታ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ተቋም 15 የሚሆኑ ትራክተሮች፣ በሞኢንኮ ኢንተርናሽናል 10 ማጨጃ እና መውቂያ ማሽኖች እንዲሁም በቢሾፍቱ ሐግቤህ ተቋም 14 ኤክስካቫተሮችን አስረክቧል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዘመናዊ የእርሻ ማሽኖችን በማቅረብ የግብርና ዘርፉን እየደገፈ መሆኑን እና የማዕድን ዘርፉን ለማሳደግም በርካታ ስራ እየሰራ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ገልፀዋል።

በሊዝ ፋይናንሲንግ ደንበኞች 20 በመቶ ተቀማጭ በማድረግ 80 በመቶ በባንኩ ተሸፍኖላቸው የተለያዩ ማሽኖችን እንዲገዙ ተመቻችቷልም ብለዋል፡፡
ርክክቡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተፈጽሟል፡፡
በየአብስራ ሚሊዮን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












