አዲስ አበባ | ህዳር 27፤ 2016| NBC ETHIOPIA- ስኮት ማክቶሚናይ ቀላል ልምምድ መስራታቸው ቼልሲን እንዲያሸንፉ እንደረዳቸው ተናግሯል።

ስኮትላንዳዊው የመሀል ሜዳ ተጨዋች፣ ማንችስተር ዩናይትድ ትላንት ምሽት በ15ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር የፖቼቲኖን ቼልሲ 2-1 ሲያሸንፍ ሁለቱንም ጎሎች ማስቆጠሩ ይታወሳል።
አማዞን ፕራይም የድላችሁ ሚስጥር ምንድን ነው ? ብሎ ላቀረበለት ጥያቄ፣ “የጨዋታ አቀራረብ መንገዳችንና ቀለል ያለ ልምምድ መስራታችን” የሚል ምላሽ ሰጥቷል።
ይህን መንገድ መምረጣቸው ወደፊት ላሉባቸው በርካታ ጨዋታዎች ጉልበት ቆጥበው ተጋጣሚዎቻቸው ላይ ጫና ለመፍጠር እንድሚያስችላቸው አስገንዝቧል።
ሆላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ፣ ግልጽ የጨዋታ ዘይቤ የላቸውም በሚል ከሚቀርብባቸው ወቀሳ በተጨማሪ በከበባድ ስልጠናዎች የተጨዋቾችን ጉልበት ይበዘብዛሉ ተብለውም ይታማሉ።
ይህ ጉዳይ በተለይም ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በስፋት እየተራገበ ያለና ክለቡ ከሚዲያዎች ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ይገባ ዘንድ ምክንያት የሆነ ነው።
የውድድር አመቱ ዘጠነኛ የሊግ ድላቸውን ያስመዘገቡበት የትላንት ምሽቱ ዉጤት በጥቂቱም ቢሆን አሰልጣኙን ከሸክማቸው ያሳርፋቸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












