አዲስ አበባ | ህዳር 28፤ 2016| NBC ETHIOPIA- የኢንተርፕሪነሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የአለም አቀፍ የኢንተርፕርነርሺፕ ሳምንትን የማጠቃለያ መርሀግብር አከናውኗል።

በአገር አቀፍ ደረጃ ክህዳር 24-28 “ለኢንተርፕሪነሮች ‘ክፍት ይሁኑ በሮች በሚል ቃል ለ8ተኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው ሳምንት በትምህርት፣ በአካታችነት፤ በስነ-ምህዳር እና ፖሊሲ ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል።
የኢንተርፕራይዞች ልማት ኢንስቲዩት ዋና ዳይሬክተር ሀሰን ሁሴን(ዶ/ር) ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለሴቶች፣ለወጣቶች፣ ለመምህራን እንዲሁም ለበርካቶች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል።
ለስራ ፈጣሪዎች ብድር በመስጠት፣ ድጎማ በማድረግ፣ የእውቀት ልውውጥ የሚያገኙበት እና የተለያዩ እድሎችን በማመቻቸት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በመድረኩ ሥራ ፈጣሪዎች ይዘዋቸው የመጡ የስራ እድሎችን አቅርበዋል።
እንደ ኢትዩጵያ ያለውን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍና ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢንተርፕሩነሮችን በመፍጠር ረገድ በርካታ ተግባራት መከናወናቸው በመድረኩ ተነስቷል።
ሰላማዊት ወንድወሰን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv












