አዲስ አበባ | ህዳር 24፤ 2016| NBC ETHIOPIA – የጸረ ሙስና ቀን በኢትዮጵያ “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በሕብረት እንታገል!” በሚል መሪ ቃል ለ19ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል።

በአለም ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ “Uniting the world against Corruption” በሚል መሪ ቃል በመጪው ህዳር 29 የሚከበር ይሆናል።
የገቢዎች ሚኒስቴርና ጉምሩክ ኮሚሽን ቀኑን በማስመልከት ላለፈው አንድ ወር የግንዛቤ ማስጨበጫና የተለያዩ የውይይት መርሀ ግብሮች ሲያካሂዱ ቆይተዋል።
በዛሬው እለት በተዘጋጀው የማጠቃለያ መርሃ ግብር በቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ አንዱ ሙስናን የመግቻ መንገድ በሆነው የሀብት ማስመዝገብ እስካሁን ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎች ንብረታቸውን ማስመዝገባቸው ተገልጿል።
የገቢዎች ሚኒስትሯ አይናለም ንጉሴ መስሪያ ቤታቸው በ2022 የያዘው ሀገራዊ ወጪን በሀገራዊ ገቢ የመተካት ራዕይ በሙስና እየተፈተነ መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ሙስናን ለመግታት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆናቸውን በመግለጽ
የጸረ ሙስና ቀን መከበርም ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።
በርካታ የዓለም ሀገራት የተባበሩት መንግስታት ዓለም ዓቀፍ የጸረ ሙስና የቃል ኪዳን ስምምነት ሰነድን እ.ኤ.አ 2003 መፈረማቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያም ህዳር 26, 2007 ስምምነቱን አጽድቃለች።
የጸረ ሙስና ቀን ሙስናን ለመግታት ሀገራት የሚወስዱት የተናጠል እርምጃ አመርቂ ውጤት ማምጣት ባለመቻሉ በጋራ ለመታገል በማለም የተጀመረ ነው።
መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv