አዲስ አበባ | ህዳር 25፤ 2016| NBC ETHIOPIA –በሰሜን ታንዛኒያ ሃናንግ በተባለችው ከተማ በደረሰ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 63 የደረሰ ሲሆን 116 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል እንዲሁም በመኖሪያ ቤቶች፣ መሰረተ ልማቶች እና የእርሻ መሬቶች ጉዳት አድርሷል።

የታንዛኒያ መንግስት 400 የነፍስ አድን ሰራተኞች ወደ ሰሜናዊው ሃናንግ ወረዳ መላካቸውን አስታውቋል።
የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ ዙሁራ ዩኑስ በሰጡት መግለጫ ሆኖም የነፍስ አድን ሰራተኞች እንደ ቴሌኮሙኒኬሽን እና የተዘጉ እና የተበላሹ መንገዶች ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ በጎርፍ እና በመሬት መንሸራተት ለተገደሉት ሰዎች የቀብር ወጪ መንግስታቸው እንዲከፍል ማዘዛቸውን ወይዘሮ ዩኑስ ተናግረዋል። መንግስት ለቆሰሉት የሆስፒታል ክፍያ እና ቤታቸው በጎርፍ አደጋው ላጡ በጊዜያዊ መኖሪያ ቤት እንዲሰጥ አዘዋል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን በአደጋው ምክንያት በዱባይ እየተካሄደ ያለውን የአየር ንብረት ጉባዔ አቋርጠው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
የጎርፍ መጥለቅለቅ በታንዛኒያ ትልቁ የተፈጥሮ አደጋ ሲሆን በየዓመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ይጎዳል።
ባለፈው ወር በዋና ከተማዋ ዳሬሰላም እና በአንዳንድ አካባቢዎች ከወትሮው በላይ የጣለው ዝናብ የሰዎች ህይወት ላይ ሞት አደጋ እና የንብረት ውድመት ማድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












