አዲስ አበባ | ህዳር 21፤ 2016| NBC ETHIOPIA -የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች የደም ስኳር መጠንን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው፡፡የስኳር በሽታላለባቸው ሰዎች አንዳንድ ምግቦች ከፍተኛ ፕሮቲን፣ አነስተኛ የስኳር ያላችው ጠቃሚ ናቸው፡፡አመጋገብዎ የስኳር በሽታን በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ ትልቅ ሚና አለው።
ሁለቱም ዓይነት ስኳር 1 እና 2 ህመምተኞች ምርጥ ምግቦች ከታች ተዘርዝረዋል።
1. ስብ ያለው ዓሳ

ሳልሞን፣ ሰርዲን፣ ሄሪንግ፣ አንቾቪ እና ማኬሬል ለልብ ጤና ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸውን የኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ ዲኤኤ እና ኢፒኤ ምንጭ ሲሆን ዓሳ ከፍተኛ ጥራት ያለው ፕሮቲን ምንጭ ነው ይህም የደም ስኳር መጠን እንዲረጋጋ ይረዳል፡፡
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሰባ ዓሳን አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች እንደ ልብ ድካም ያሉ ለድንገተኛ የልብ ህመም (coronary syndromes) የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ እና በልብ በሽታ የመሞት እድላቸው አነስተኛ ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሰባ ዓሳ መመገብ የደም ስኳርን ለመቆጣጠርም ይረዳል።
ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው 68 ጎልማሶችን ያሳተፈ ጥናት እንደሚያሳየው የሰባ ዓሳን የበሉ ከምግብ በኋላ ባለው የደም ስኳር መጠን ላይ ጉልህ የሆነ መሻሻሎች ነበራቸው ።
2 አረንጓዴ ቅጠሎች (Leafy greens)

በተጨማሪም በቀላሉ ሊፈጩ የሚችሉ ካርቦሃይድሬትስ ወይም በሰውነት ውስጥ የሚወሰዱ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በእጅጉ አይጎዱም። ስፒናች፣ ጎመን እና ሌሎች ቅጠላ ቅጠሎች ቫይታሚን ሲን ጨምሮ የበርካታ ቪታሚኖች እና ማዕድናት ምንጭ ናቸው።
3. አቮካዶ

አቮካዶ ከ 1 ግራም ያነሰ ስኳር፣ ጥቂት ካርቦሃይድሬትስ፣ ከፍተኛ ፋይበር እና ጤናማ ቅባቶች ስላሉት የደምዎን የስኳር መጠን ስለሚያሳድግ ጠቀሜታ አለው።
4. ባቄላ

ባቄላ ዋጋው ተመጣጣኝ፣ ገንቢ እና እጅግ በጣም ጤናማ ነው። ባቄላ በቫይታሚን ቢ፣ ጠቃሚ ማዕድናት (ካልሲየም፣ ፖታሲየም እና ማግኒዚየም) እና ፋይበር የበለፀገ የጥራጥሬ አይነት ነው።
ለከፍተኛ የልብና የደም ሥር (cardiovascular) ሕመም የተጋለጡ ከ3,000 በላይ ተሳታፊዎችን ባሳተፈ ጥናት፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ጥራጥሬ ያላቸው እህል የሚመግቡ ሰዎች ሰዎች ዓይነት 2 የስኳር በሽታ የመያዝ እድላቸው ቀንሷል።
5. ብሮኮሊ

ብሮኮሊ በጣም ጠቃሚ ከሆኑ አትክልቶች አንዱ ነው። ብሮኮሊ የደምዎን የስኳር መጠን ለመቆጣጠርም ይረዳል፡፡
6. እንጆሪ

እንጆሪ ቀይ ቀለማቸውን የሚሰጣቸው አንቶሲያኒን በመባል የሚታወቁ ፀረ-ባክቴሪያዎች የያዙ ናቸው።
እ.ኤ.አ. በ 2017 የተደረገ ጥናት እንዳመለከተው ከመጠን በላይ ውፍረት እና የስኳር በሽታ ባለባቸው ሰዎች ለ6-ሳምንት የእንጆሪ እና ክራንቤሪ (cranberries) ጭማቂ ሲጠጡ የኢንሱሊን መጠናቸው መሻሻል አሳይቷል።
ምንጭ (Healthline)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












