Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ሙሽራው ሙሽሪትን ገደለ

November 28, 2023
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ህዳር 18፤ 2016| NBC ETHIOPIA – አንድ ታይላንዳዊ የቀድሞ ወታደር በሠርጉ ዕለት ሙሽራዋን እና ሌሎች ሦስት ሰዎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ።

የ29 ዓመቱ ሙሽራ ቻቱሮንግ ሱክሱክ እና የ44 ዓመቷ ሙሽራ ካንቻና ፓቹንቱክ ጋብቻቸውን ባለፈው ቅዳሜ በሰሜናዊ ምሥራቅ ታይላንድ ውስጥ ነበር የፈጸሙት።

ሙሽራው የሠርጉ ድግስ እየተካሄደ ሳለ በድንገት ተነስቶ በመውጣት ሽጉጥ ይዞ ተመልሶ ነው ጥቃቱን የፈጸመው። በዚህም ሚስቱን፣ የ62 ዓመቷን የሙሽራዋን እናት እና እህቷን ከገደለ በኋላ እራሱን እንዳጠፋ ቢቢሲ ዘግቧል።

በተጨማሪም ሙሽራው የተኮሳቸው ተባራሪ ጥይቶች ሁለት የሠርጉ ሥነ- ሥርዓት ታዳሚዎችን ያቆሰለ ሲሆን፣ ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ የአንደኛው ግለሰብ ሕይወት አልፏል።

ፖሊስ ለቢቢሲ እንደገለጸው ሙሽራው በወቅቱ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር ነገር ግን ግድያውን ለመፈጸሙ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም ብሏል።

የታይላንድ መገናኛ ብዙኃን ለፖሊስ ቃላቸውን የሰጡ የሠርጉ ታዳሚዎችን ጠቅሰው እንደዘገቡት፣ ከጥቃቱ ቀደም ብሎ በሠርጉ ሥነ ሥርዓት ላይ በሙሽሮቹ መካከል ጭቅጭቅ ነበረ። እንዲሁም ሙሽራው በእሱ እና በሚስቱ መካከል ባለው የዕድሜ ልዩነት ምክንያት ጥሩ ስሜት ይሰማው እንዳልነበረም ተናግረዋል።

ነገር ግን ፖሊስ እየተባሉ ያሉት ነገሮች ሁሉ ከግምት የዘለሉ እንዳልሆኑ እና አስፈላጊውን ማስረጃ በመሰብሰባቸው ጉዳዩ በቅርቡ እንደሚዘጋ ገልጿል።

የታይላንድ መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ሙሽራው እና ሙሽሪት ባለፈው ቅዳሜ ይፋዊ የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን ከማከናወናቸው በፊት ለሦስት ዓመታት አብረው ኖረዋል።

የቀድሞ የአገሪቱ ሠራዊት አባል የነበረው ሙሽራው በውትድርና አገልግሎቱ ወቅት በደረሰበት ጉዳት ቀኝ እግሩን ያጣ ሲሆን፣ በአካል ጉዳተኞች ስፖርት ውስጥ በመሳተፍ ይታወቃል።

ባለፈው ዓመት በኢንዶኔዢያ በተካሄደው የእስያ የአካል ጉዳተኞች የስፖርት ውድድር ላይ በውሃ ዋና ተወዳድሮ የብር ሜዳሊያን ለማግኘት ችሏል። በሚቀጥለው ወር ታይላንድ በምታስተናግደው የዓለም የአካል ጉዳተኞች ስፖርት ውድድር ላይ ከሚሳተፉ አትሌቶች መካከል አንዱ እንደሚሆን ይጠበቅ ነበር።

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc

Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

Next Post

ታሪክ ሲጨለፍ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ታሪክ ሲጨለፍ

ታሪክ ሲጨለፍ

የገቢዎች ሚኒስትር ባለፉት ሩብ አመት የስራ ጊዜ ውስጥ 193 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 98 በመቶ ማሳካቱን አስታውቋል

የገቢዎች ሚኒስትር ባለፉት ሩብ አመት የስራ ጊዜ ውስጥ 193 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 98 በመቶ ማሳካቱን አስታውቋል

የልጆችን የቋንቋ እድገት ችግሮች መለየት

የልጆችን የቋንቋ እድገት ችግሮች መለየት

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?