አዲስ አበባ | ህዳር 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ከ28ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ግለሰብ ተይዞ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ ።

ተጠርጣሪው በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2- C 32496 አ/አ በሆነ ተሽከርካሪ ውስጥ 284 ባለ መቶ ኖቶች(28 ሺህ 400) ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር ይዞ ሲንቀሳቀስ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 መክሊት ህንፃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር ውሏል ።
በተሽከርካሪው ውስጥ በተደረገ ፍተሻ ከሃሰተኛ ዶላር በተጨማሪ ስታር ሽጉጥ ከ 8 ጥይቶች ጋር ተይዞ ምርመራ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል ።
ሀሰተኛ ገንዘቦችን በማተምና ወደ ገበያ ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ የሚፈፀም ወንጀል በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ ይህንን ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት
የሚሰጠውን መረጃና ጥቆማ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












