አዲስ አበባ | ህዳር 17፤ 2016| NBC ETHIOPIA – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ20ኛው የተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ድርጅት ጉባዔ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር አድረገዋል፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያን ያለፉት አምስት አመታት የፖሊሲ ለውጥ፣ በብዝሃ ዘርፍ እድገት የተደረገ ኢንቨስትመንት፣ ለአረንጓዴ ልማት እና ንፁህ የኃይል ምንጭ የተሰጠውን ትኩረት ብሎም ለማኅበራዊ ልማት ስራ የተደረገውን አፅንዖት አንስተዋል።
በዚህም ላይ ተመስርተው ሁሉን አካታች ለሆነ ዘላቂ የኢንደስትሪ ልማት ጥሪ ማቅረባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












