አዲስ አበባ | ህዳር 07 2016| NBC ETHIOPIA -የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም፣ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊና የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ በተመለከተ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

አምባሳደር መለስ ዓለም በዚሁ ጊዜ የዓለም የጥቁር ህዝቦች የታሪክ የቅርስና የትምህርት ማዕከል በኢትዮጵያ ሊከፈት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ማዕከሉ በአሜሪካ ካሪቢያንና በሌሎች ዓለም ላይ ያሉ ጥቁር ህዝቦች የጥናት ምርምር ተቋማትን ያቀፈ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡
ማዕከሉ በመጪው ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ዋና መቀመጫውን ኢትዮጵያ ማድረጉን በይፋ ያሳውቃል ብለዋል።
ይሄም ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች ቤት፤ አዲስ አበባ ደግሞ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን የሚያፀና መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ፣ በቀኝ ግዛት ያልተያዘች፣ የስልጣኔ ማዕከል መሆኗ ለማዕከሉ መቀመጫነት እንድትመረጥ አድርጓታል በተጨማሪም ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል ያላት፣ እንደ ፖስታ ማህበር፣ የገለልተኛ ሀገሮች ንቅናቄ፣ የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እና መሰል ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ድርጅቶች መስራች መሆኗም ተመራጭ እንድትሆን አድርጓታል ነው ያሉት፡፡
አምባሳደር መለስ አክለውም በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) እና በሱዳን ሪፐብሊክ ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ ለሱዳን ወንድም ህዝብ ሰላም እና መረጋጋት ቁርጠኛ መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv