አዲስ አበባ | ህዳር 04 2016| NBC ETHIOPIA – የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።

የምክር ቤቱ አባላት ካቀረቡት ጥያቄዎች መካከል
በአማራ ክልል አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታን፣በኮማንድ ፖስቱ በክልሉ እየመጡ ያሉ ለውጦች፣ በህግ ማስከበር ሂደት ሰላማዊ ዜጎች እንዳይጎዱ የተሰሩ ስራዎችንና የክልሉ ህዝብ የሚያነሳቸው ጥያቆዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የተከናወኑ ተግባራት፣ በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያና በአማራ ክልል የተፈጠሩት ችግሮች በአጭር ጊዜ እንዲቋጩ መንግስት ምን እየሰራ ነው?
የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የጎረቤት አገራት ማዕከል ጤናማነትና ቅድሚያ የሚሰጥ ነው፡፡ በመሆኑም ከወደብ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ከተነሳው ጥያቄ ጋር ተያይዞ በአሉታዊ የሚተነተኑ አገራት እየተስተዋሉ ነው። ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ ያላት ግንኙነት ምን ይመስላል?
አሁን በኢትዮጵያ በሚታዩ ችግሮች የውጭ ሀይሎች እጃቸው እንዳለበት ይነገራል፤ ይህን ጣልቃ ገብነትን ለመከላከል እና እነዚህን አደብ ለማስገዛት መንግስት ምን እየሰራ ነው የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል?
በተመሳሳይም በህብረተሰቡ ተጀምረው ያላለቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች የመብራት የውሃ ፕሮጀክቶች ላይ ጥያቄ አለው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ከመጨረስና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመስራት ላይ ማብራሪያ ቢሰጡ፣ በህብረተሰቡ ተጀምረው ያላለቁ የመንገድ የመብራት የውሃ ፕሮጀክቶች፤ ሀገራዊ ምክክሩ መዘግየት፤ የኑሮ ውድነት የሚሉ ይገኙበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












