1. አውስትራሊያ ፣ታላቁ ባሪየር ሪፍ(The Great Barrier Reef)

የአለማችን ትልቁ coral reef system አስደናቂ ውበት የሚመለከቱበት የውሃ ውስጥ አለምን የሚያስሱበት፣ በቀለማት ያሸበረቁ የኮራል ቅርፆች (coral formations) መካከል መዋኘት(snorkel) ፣ አሳ፣ ኤሊዎችን እና ዶልፊኖችን ጨምሮ የተለያዩ የባህር ወስጥ ህይወትን የሚመለከቱበት ስፍራ ነው።
2. ግብፅ ፣ ፒራሚዶች

የግብፅ ፒራሚዶች ከጥንት የአለም ድንቃ ድንቅ ስራዎች መሀከል ሲሆኑ ከብዙ ሺህ አመታት በፊት በግብፅ ንጉሶች ፈርኦኖች የተገነቡትን በኩራት የቆሙ ህንጻዎች የሚመለከቱበት የስፊንክስን እንቆቅልሽ የሚያዩበት ወደ ጥንታዊ ግብፅ በምናብ የሚወስዳችሁ አስደናቂ ታሪካዊ ቦታ ነው።
3. ታንዛኒያ ፣ የሴሬንጌቲ ብሔራዊ ፓርክ,

በየሜዳው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዱር አራዊትና የሜዳ አህዮች በብዛት በየሜዳው ሲያልፉ ማየት ፣ ግርማ ሞገስ የተላበሱ አንበሶችን፣ ዝሆኖችን፣ ቀጭኔዎችን እና እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ሌሎች የዱር አራዊትን በተፈጥሮ መኖሪያቸው ውስጥ የሚያገኙበት አስደናቂ ስፍራ ነው።
4. ኖርዌይ ፣ ሰሜናዊው መብራቶች (The Northern Lights)

አውሮራ ቦሪያሊስ በመባልም በሚታወቀው የሰሜናዊ ብርሃን ሚስጥራዊ ውበት ለመማረክ ይዘጋጁ። በክረምቱ ወራት በሌሊት ሰማይ ላይ የሚያማምሩ የብርሃን መብራቶችን ዳንስ ለማየት ወደ ኖርዌይ አርክቲክ ክልሎች፣ እንደ ትሮምሶ ወይም ሎፎተን (Tromsø or Lofoten) መሄድ ይኖርባችኋል።
5. ህንድ ፣ ታጅ ማሃል

በህንድ አግራ የሚገኘውን የፍቅር ተምሳሌት የሆነውን ታጅ ማሃልን በህይወት እያሉ መጉብኝት ያለቦት ስፍራ ነው።በዚህ አስደናቂ መካነ መቃብር አስደናቂ የስነ-ህንፃ ጥበብ ያያሉ፡፡
እነዚህ አምስት መዳረሻዎች በእርግጠኝነት መጓዝ የሚወዱ ሰዎች በህይወት እያሉ መመልከት ያለባቸው የአለማችን ድንቅ ስፍራዎች ናቸው፡፡
እነዚህን አስደናቂ የአለም ድንቆች ለማየት እድሉን እንዳያመልጥዎት!!!!!
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












