አዲስ አበባ | ጥቅምት 23 2016| NBC ETHIOPIA – የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የ2016 የ1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ዉይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ልማትን በማዳከም የሀገር ኢኮኖሚ እንዲገታ የሚያደርገዉን ሙስና ጉዳቱንና አደገኝነቱን በመገንዘብ ለከተማ አስተዳደሩ ልማትና በጎ ተግባር እንቅፋት እንዳይሆን አፅንኦት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ኮሚሽኑ ገልጿል።
በሩብ አመቱ በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ የዳነ የመንግስትና የህዝብ ሀብት በገንዝብ 126,762,211 ሲሆን በአይነት 170 ጠቅላላ ንብረት ማዳን ተችሏል። 12 ግለሰቦች ደግሞ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተለይተዋል።

በ2025 ከሙስና የፀዳች ከተማን ለመፍጠር አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፀዉ ኮሚሽኑ በተያዘዉ በጀት አመት በስሩ የሚገኙ አመራሮች የሀብት ምዝገባ እንዲያደርጉ ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እየሰራሁ ነዉ ብሏል።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












