አዲስ አበባ | ጥቅምት 26 2016| NBC ETHIOPIA – ቢ.ኤም.ኢ.ቲ ኢነርጂ ፣ ቴሌኮም፣ ኢንዲስትሪ፣ እና ንግድ ኃ.የተ.የግል.ማኅበር ለደንበኞቹ በሚያቀርባቸው የኤሌክትሪክ እና ቴሌኮም ኬብሎች ከተመሳሳይ ምርቶች የሚለይበትን አዲስ የአስተሻሸግ ዲዛይን ይፍ አድርጓል።

በተመሳሳይ የሚሰሩ ሀሰተኛ የኬብል አይነቶች በተቋሙ ስም ለገበያ በስፋት እየቀረቡ መሆናቸውን ተከትሎ አዲስ የአስተሻሸግ ለውጥ ለማድረግ መገደዱን የተቋሙ ም/ክ ስራ አስኪያጅ ኢምራን ሙሄ ገልፀዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ተመሳስለው የሚሰሩ እና ለገበያ የሚቀርቡ የኬብል ምርቶች በሰው ህይወት እንዲሁም በሀገር የኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚያደርሰው ተፅእኖ ከፍተኛ በመሆኑ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ የቁጥጥር ስራዎችን እንዳረገ ይገኛል ብለዋል።
ደንበኞች በተቋሙ ሀሰተኛ የኬብል ምርቶች እንዳይሸወዱ በምርቶቹ እሽግ ላይ በአንድ ሜትር ልዩነት የተቋሙ ስያሜን የታተመበት ሲሆን በእሽጉ ላይ የሚገኘውን የኪው አር ኮድ በመጠቀም የምርቱን ኦርጅናልነት ማረጋገጥ እንደሚችሉ ም/ክ ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
በገበያ ላይ የሚገኙት የኬቤል ምርቶች ጥራታቸውን ያልጠበቁ እና የተለያዩ ችግሮችን የሚያስከትሉ በመሆኑ ደንበኞች እንዲሁም አከፋፋዮች ትክክለኛውን የቢ.ኤም.ኢ.ቲ ኬብል ምርቶችን እንዲገዙ ጥሪ ቀርቧል።
ቢ.ኤም.ኢ.ቲ ኢነርጂ ፣ ቴሌኮም፣ ኢንዲስትሪ፣ እና ንግድ ኃ.የተ.የግል.ማኅበር ከ10 አመታት በላይ የኢነርጂ እና ቴሌኮም ኬብሎች እያመረተ ለገበያ ሲያቀር ቆይቷል።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












