አዲስ አበባ | ጥቅምት 01 2016| NBC ETHIOPIA – የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአጋር አካላት ጋር በትብብር የሚያዘጋጀው 17ኛው የ”ኢትዮ-ኮን” ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኤግዚቢሽን መካሄድ ጀምሯል።

ኤግዚቢሽኑ የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች የዘመኑ ቴክኖሎጂና የአሰራር ሥርዓት የደረሰበትን ደረጃ በአንድ ስፍራ ለማየትና ለመገብየት የሚያስችል መድረክ ይፈጥራል ተብሏል።
ላለፉት ሶስት አመታት በኮቪድ 19 ወረርሽኝና በሃገሪቱ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ ተቋርጦ የነበረው ኦግዚቢሽኑ በኤግዚቢሽን ማዕከል በሚኖረው ቆይታ በተለያዩ የግንባታ ቁሶች ገጠማ ላይ የሚያተኩር የስልጠና መድረክ ይኖረዋል።
ዛሬን ጨምሮ ለአራት ቀናት በሚቆየው ኤግዚቢሽኑ የኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጮች ወሳኝ በሆነ የዘርፉ የአሰራር ስርዓት ላይ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሏል።
በመቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv