አዲስ አበባ | መስከረም 24 2016| NBC ETHIOPIA – የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል አባገዳዎች ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ በአዲስ አበባና በቢሾፍቱ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ ፈጣሪውን የሚያመሰግንብት፣ የእርቅና የይቅርታ በዓል ነው።
የኦሮሚያ ክልል፣ የአዲስ አበባና የፌዴራል ጸጥታ አካላት በዓሉ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገዋል።
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አስፈላጊው ውይይትና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሠራታቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ የአዲስ አበባ ከተማ፣ የሸገርና የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች እንግዶቻቸውን ለመቀበል ዝግጅታቸውን አጠናቀዋልም ብለዋል።
በዓሉ ያለምንም ፖለቲካዊ አመለካከት ልዩነት በአንድነት የሚከበር መሆኑን ጠቁመው፤ በበዓሉ ላይ ከአባገዳ ዓርማ ውጭ የትኛውንም መለያ ይዞ መሄድ እንደማይቻል በመግለጫው አመላክተዋል።
ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ህዝቡን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረቡን ኢ ፕ ድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












