አዲስ አበባ | መስከረም 23 2016| NBC ETHIOPIA-የአርሰናል አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ ትላንት ምሽት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በሌንስ ሁለት ለአንድ በተረቱበት ጨዋታ ቡካዮ ሳካን በማሰለፋቸው እንደማይቆጩ ተናግረዋል።

የ22 አመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ በጡንቻ ጉዳት ሳቢያ በ34ኛው ደቂቃ ከሜዳ መውጣቱ አይዘነጋም።
አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ የቡካዮ ሳካን ጉዳት “አስፈሪ” ብለው ገልጸውታል። ይሁንና “ተጨዋቹን በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ በማካተቴ አንዳች ጸጸት አይሰማኝም” ባይ ናቸው።
ሳካ እንደሌሎች ቀናት ሁሉ በሙሉ ጤንነት ወደ ሜዳ እንደገባም አስረድተዋል።
ስለጉዳቱ በዝርዝር ባያብራሩም በተረከዙ ኳስ ሲቀበል እንዳጋጣመው ጠቁመዋል።

ቡካዮ ሳካ በምሽቱ ጨዋታ ለጋብሬል ሄሱስ ለጎል የምትሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበሉ ይታወሳል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት