አዲስ አበባ | መስከረም 22 2016| NBC ETHIOPIA- የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

ኢኒሼቲቩ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ሶማሊያን፣ ጂቡቲን፣ ኤርትራን፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን በአባልነት ያቀፈ ሲሆን ከየካቲት 2015 ዓ.ም ጀምሮ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭን ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት እየመራች ትገኛለች።
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 18ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ የኢኒሼቲቩ ሊቀመንበር እና የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ተገኝተዋል።
የአውሮፓ ሕብረት ዓለም አቀፍ የትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፣ የኢኒሼቲቩ አባል አገራት ሚኒስትሮችና የልማት አጋሮች ተወካዮችም ታድመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












