አዲስ አበባ | መስከረም 22 2016| NBC ETHIOPIA -“አንድ ቤተሰብ ፤ ለአንድ ህፃን” በሚል መሪ ቃል 100 ህፃናትን እስከ ዩኒቨርስቲ ድረስ ለማስተማርና ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መርሃ ግብር አካሂደናል።

እናት ልጇ በአካል እና በአዕምሮ ሲያድግና ሲጎለብት ከማየት በላይ የሚያስደስታት ጉዳይ የለምና እድሉን ያገኛችሁ ወላጆች እንኳን ደስ አላችሁ::
በመንግስት በተያዘው ትውልድን የመገንባት መርሃ ግብር መሰረት በከተማችን ልዩ ትኩረት ሰጥተን በመሰራት ላይ ያለን ሲሆን፣ ትውልድ ላይ ኢንቨስት ማድረግ የነገ የሃገር ተስፋን ዛሬ መስራት በመሆኑ “አዲስ አበባን ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ የአፍሪካ ከተማ “ለማድረግ ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን::

ዛሬ 100 (አንድ መቶ) ህፃናትን እስከ ዩኒቨርሲቲ ድረስ ለማስተማርና ለመደገፍ ኃላፊነት የወሰዱት አቶ ማናዬ ሰንደቁ የከተማችንን በጎ ራዕይ በመጋራት ይህንን ትልቅ ሀላፊነት በመረከባቸዉ በወላጆቹና በህፃናቱ ስም እናመሰግናቸዋለን።
በአጠቃላይ በ2013 እና የዛሬውን ጨምሮ በበጎ ፍቃደኞች ብቻ 750 ህፃናት ተጠቃሚ ሆነዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












