አዲስ አበባ | መስከረም 22 2016| NBC ETHIOPIA -የውጭ አገራት የስራ ስምሪት የሀገርን ፍላጎትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ከተለያዩ አገራት ጋር እየሰራ መሆኑን የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።



ሁለተኛው አህጉር አቀፍ የአፍሪካ የሰው ሃብት ልማትና የስራ እድል ፈጠራ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት ሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ተሻለ በሬቻ፤ ከአገር ውስጥ በተጨማሪ የውጭ አገራት የስራ ስምሪት ላይ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
በውጭ አገራት የስራ ስምሪቱ የሀገርን ፍላጎትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ከተለያዩ አገራት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ብለዋል።
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፤ ኢትዮጵያ ትኩረት ከምትሰጣቸው የልማት መስኮች መካከል የሰው ሀብት ልማት አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የክህሎት ልማት ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢና የዘ-አይ ካፒታል ኢንስቲትዩት ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ገመቹ ዋቅቶላ፤ በውጭ አገራት የስራ ስምሪት ዜጎች ተጠቃሚ እንዲሁኑ ሙያና ክህሎት ላይ መስራት ይገባል ብለዋል።
የጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ድርጅት (ጂ.አይ.ዜድ) የኢትዮ-ጀርመን ዘላቂ የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራም ማናጀር ላሪስ ፊቼል፤ ጀርመን የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን ለማጎልበትና በስራ እድል ፈጠራ ለኢትዮጵያ ድጋፍና ትብብሯን አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/