አዲስ አበባ | መስከረም 18 2016| NBC ETHIOPIA -በጉዳት ሳቢያ ለወራት ከእግር ኳስ ርቆ የነበረው ጀርመናዊው የባየር ሙኒክ ግብ ጠባቂ ማኑኤል ኑኤር ወደ ልምምድ ተመልሷል፡፡

የ37 ዓመቱ ነኤር በበረዶ መንሸራተት ስፖርት ላይ በተሳተፈበት ወቅት ባጋጠመው አደጋ ሳቢያ እግሩ ላይ ጉዳት ማስተናገዱ አይዘነጋም፡፡
ከባየር ሙኒክ ጋር የሁለት ጊዜያት የአውሮፓ ቻምየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ያሸነፈው ማኑኤል ኑኤር እግሩ ላይ ቀዶ ህክምና እንደተደረገለትና ከቀሪ የ2022/23 የውድድር ዓመት ውጪ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይሁንና ተጨዋቹ ከወራት በኋላ ከጉዳቱ በማገገሙ ወደ ዋናው መደበኛ ልምምድ በመመለስ ከጎል ዘብ አጋሮቹ ስቬን ኡልሬሽና ዳንኤል ፔሬትዝ ጋር ልምምዶችን ማከናወኑ ተገልጿል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://nbcethiopia.com/news/
Telegram- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/