አዲስ አበባ | መስከረም 18 2016| NBC ETHIOPIA -የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሰጠው ድጋፍ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተካሄደ፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ ልዑካን ቡድን አባላት ለኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚሰጠው ድጋፍ እያመጣ ያለው ለውጥ ላይም መክረዋል፡፡
በውይይቱ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሂደትና አሁናዊ ሁኔታ፣ መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ እየተከተለ ያለውን አቅጣጫና ዘርፉን የተሻለ ለማድረግ በሚደረገው ርብርብ ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም የመጡ ለውጦችን በሚመለከት ለልዑካን ቡድኑ ገለጻ ተደርጓል፡፡
እንደ ኢፕድ ዘገባ ልዑኩ የይርጋለም የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክንና የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮችንም ጎብኝቷል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












