


አዲስ አበባ | መስከረም 15 2016| NBC ETHIOPIA- ከመስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብልጽግና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።
በማጠቃለያ መድረኩም የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የስልጠናውን ማጠቃለያና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በሚመለከት የስራ ስምሪት ሰጥተዋል።
ስልጠናው ወሳኝ በሆኑ ሃገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የፈጠረ ሲሆን ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ሁለት ሺህ የፓርቲው አመራሮች ተሳትፈዋል።
እንደ ኢፕድ ዘገባ የአቅም ግንባታ ስልጠናው በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች በቀጣይነት እንደሚሰጥ ፓርቲው ገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv










