Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት…

September 27, 2023
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | መስከረም 16 2016| NBC ETHIOPIA -ደመራ፣ መደመር፣ ደመረ፣ አከማቸ ማለት ነው፡፡ ደመራ የመለወጥ ምልክትነትም ነው፡፡ ለወንጀለኞች ስቅላት ይውል የነበረ መስቀል ዋጋና ምልክቱ የተለወጠበት ነው፡፡ ደመራ ብዙ ሰዎችን ሰብስቦ በኅብረት የሚያቆም ነው፡፡ ደመራ ባነሰው ላይ መጨመር ነው፡፡ ደመራ የተበተነውን መሰብሰብ ነው፡፡ የተዘረዘረ ነገርን የሚደምርና የሚያገናኝ ነው፡፡

ጸጋዬ ገ/መድኅን በግጥሙ…

ነጋ አዲስ ዘመን ችቦ፤

ምድር ሕይወት አፈለቀች፤

የምሥራች አዝርዕቷን፤ አዲስ ቡቃያ ወለደች፤

የአደይ አበባን ለገሰች፣

ለአዲስ ዘመን አዲስ ብርሃን፤ አዲስ መስከረም ገበየች፣

…እንዳለው የአዲስ ዘመን ችቦ በአዲስ የፈካ ዘመን የሚጀመርበት ነው፡፡ የሰዎችም አዲስ ተስፋ አዲስ ጅምር የሚታይበት ነው፡፡ የመስቀል ወፍ የምትታሰርበት፤ አዝዕርት የሚበቅልበትም ነው፡፡

ደመራ ለበዓለ መስቀል ዋዜማ እንጨቶች የሚደመሩበት ነው፡፡ እንጨቶች ተሰብስበው ችቦ፤ ችቦዎች ተሰብስበው ደመራ የሚሆኑበት ነው፡፡ የችቦ እንጨቶችና ጭራሮዎች ምን ቢበዙ ወደ አንድ ካልመጡ ችቦ አይሆኑም። እንጨቶቹን የሚያስተሳሥራቸው የማሠሪያ ልጥ አለ፡፡

ችቦዎቹም በጋራ ተደጋግፈው ካልቆሙ ደመራ አይሆኑም። ችቦዎቹን አንድ አድርጎ የሚያቆማቸው የመሐሉ እንጨት አለ፡፡ ይህ እንጨት ጠንካራና በዙሪያው የተሰባሰቡትን ችቦዎች መሸከም የሚችል ነው፡፡ ይህ መሰሶ ኢትዮጵያን የሚወክልም ነው፡፡

የችቦው ሁሉም ጭራሮዎች አንድ ዓይነት አይደሉም፡፡ ከአንድ ቦታም አይለቀሙም፡፡ ሁሉም ችቦዎችም ተመሳሳይ አይደሉም፤ ከአንድ ቤት አይመጡም። ሁሉም እንጨቶች በየራሳቸው ይቆማሉ፤ ግን ደግሞ ብርታትና ጥንካሬ፣ ዐቅምና ጉልበት እንዲኖራቸው ችቦ ሆነው ይደመራሉ፡፡ እንጨቶቹን እንደሚያስተስሥረው ልጥ፣ ኢትዮጵያውያንን የሚያስተሣሥሩ ልዩ ልዩ ማንነቶች አሉ፡፡ ደመራ በመሰባሰብ የሀገራችንን ከፍታ እውን ለማድረግ የምንሰባሰብበት ተምሳሌታችን ነው፡፡

ኢትዮጵያ እንደ ችቦ እንጨቶች ብዙ ባህሎች፣ እምነቶች፣ ሀብቶች፣ ዕሴቶች፣ አመለካከቶች፣ ታሪኮች አሏት፡፡ ሁላችንም የግድ አንድ ዓይነት ማሰብ አይጠበቅብንም፤ የግድ ከአንድ ባህል፣ ከአንድ ቋንቋና ከአንድ ማንነት መገኘት አይኖርብንም። እነዚህን ሁሉ ጸጋዎች ከደመርናቸው፣ መጀመሪያ እንደ ችቦው አካባቢያዊ ዐቅም ይሆኑናል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ እንደ ደመራው አስተሳሥረን በአንድ ዓምድ ላይ ካቆምናቸው ትልቅ ሀገር እንገነባለን፡፡ ይህ ችቦዎቹን አንድ አድርጎ የሚያቆመው የመሐል እንጨት አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማኅበረሰብ የምንፈጥርበት የፌዴራል ሥርዓት ነው፡፡

ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነታችን ነው፡፡ በዚህ የኢትዮጵያዊነትና የኅብረ ብሔራዊ አንድነት ደመራ፣ ግርማዋ የሚያስፈራ፣ የበለጸገች፣ ጠንካራ፣ ታላቅ የጋራ ሀገር መገንባት እንችላለን፡፡ የዚህ ሁሉ ቀመሩ ግን- እንደ ደመራው፣ መደመር ነው፡፡

ችቦውን በየግልና በየአካባቢያችን ልንሠራው እንችላለን፡፡ ደመራውን ግን በጋራ ካልሆነ አንደምረውም። የመጣንበት መንገድ ለየቅል ሊሆን ይችላል፡፡ እምነታችን፣ ምርጫችንና ምኞታችንም የየብቻችን ችቦ ሊሆን ይችላል። ሀገራችን ግን የጋራችን ደመራ ናት። ያለሁላችን አትኖርም። ምን ብንጓጓ ደመራውን ቸኩለን ለብቻችን አንለኩሰውም። የግድ ሌላውን እንጠብቃለን። እንደ ሀገር እንጂ እንደ ንዑስ አከባቢ፣ ወይም እንደ ሠፈር እኔና የኔ ብቻ ማለት አንችልም። ደመራው ለሁላችን በሚሆን ሥርዓት የሚመራ የሁላችንም ሀገር መስታወት ነው፡፡

ደመራው በኔ ችቦ በኩል ቀድሞ ይለኮስልኝ አንልም። ደመራው ሲለኮስም ‹የኔ ችቦ ትቀጣጠል› ይሆን ብለን አንሠጋም። ከየትም ይጀመር ከየት፣ ሙቀትና ብርሃኑ ለሁሉም እንጨቶችና ችቦዎች በሂደት ይዳረሳል፡፡

የኢትዮጵያ ሠናይ እሳት የሆነው የኢትዮጵያ ዕድገት፣ የትም መንደድ ቢጀምር፣ በጊዜ ሂደት ለሁላችን ይደርሳል፡፡

አንዱ እንጨት ለሌላው፣ አንዱ ችቦ ሌላው ብርሃን እንዲሆን በማጋራቱ ከእርሱ የሚጎድልበት ነገር የለም፡፡ ነገር ግን የሚጨምረው ዐቅም አለ፡፡ ሁሉም እየተለኮሱ በሄዱ ቁጥር፣ የብርሃኑ ዐቅም እየጨመረ ይሄዳል፡፡

እኛም ለሌላው ወገናችን ባካፈልን ቁጥር የሚጎድልብን ነገር የለም፡፡ የኢትዮጵያ ዐቅም ግን እየጨመረ፣ እየጠነከረ ይሄዳል፡፡ ትኩረታችን የገዛናት ወይም ሠርተን ያመጣናት ችቧችን ሳትሆን ትልቁ ደመራ ነው። የበዓሉ አመስጥሮ ያለውም ከዚሁ ነው፡፡

ችቦውን ልንገዛውና ልንሸጠው እንችላለን፡፡ ደመራው ግን ልክ እንደ ኢትዮጵያ ነው። አይሸጥም አይለወጥም። ሁሉም በግል ይዤው ልሂድ አይልም። እዚያው በጋራ ደምረን፣ በጋራ ልቦናችን ይዘነው የምንሄደው – የወል እውነታችን ነው። የኛነታችን ካስማችንም ጭምር ነው፡፡

ደመራ እውነተኛው መስቀል የተገኘበት ጠቋሚ ኮምፓስ ነው፡፡ ለሀገራችን እድገትና ብልጽግና በአንድነት የመቆም ምሳሌያችን ነው፡፡ ደመራ አቅጣጫ ነው፡፡ እውነተኛው መስቀል የተለየበት፡፡ ኢትዮጵያም ልጆቿ የሚቆሙበትና የሚሄዱበት እውነተኛ አቅጣጫ ለተስፋዋ ብርሃን፣ ለጥንካሬዋም ፈለግ ይሆናታል፡፡

ልክ መስቀሉን ፈልጎ ማግኘት እጅግ ከባድ ሆኖ ጊዜ እንደወሰደው ብልጽግናን መሻትም እንዲሁ ብዙ ድካምና ጥረት ይፈልጋል፡፡ መስቀሉን ማግኘት የብዙዎችን መተባበርና ምክር እንደመፈለጉ በሀገራችን ብልጽግናን ማረጋገጥም በዚሁ ልክ መተባበርና አብሮነትን መፈለጉ ከልቦናችን ይቀመጥ፡፡

የዘንድሮውን የደመራ በዓል እነዚህን ታላላቅ ዕሳቤዎች እያሰላሰልን እንደምናከብረው ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ኢፕድ ዘግቧል፡፡

መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ለሁላችን ይሁን፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ተጠናቀቀ…

Next Post

በሱዳን ልዩ ሀይል (RSF) በተፈጸመ ጥቃት10  ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
17
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post

በሱዳን ልዩ ሀይል (RSF) በተፈጸመ ጥቃት10  ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

በኢራቅ  በተነሳ የእሳት አደጋ 100 ሰዎች ህይወታቸውን አጡ

ዜና እረፍት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?