
አዲስ አበባ | መስከረም 15 2016| NBC ETHIOPIA- ለሰባት ዓመታት ደርቆ የነበረው የጨርጨር ሃይቅ ተመልሶ ወደ ቱሪዝም መስህብነት እየተቀየረ መሆኑን የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
የጨርጨር ሃይቅ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሀብሮ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ቦኬና ኦዳ ቡልቱም ወረዳዎችንም ያዋስናቸዋል፡፡
634 ሔክታር መሬት የሚሸፍነው የጨርጨር ሀይቅ ልክ እንደ ሃረማያ ሃይቅ ደርቆ ለሰባት ዓመታት ቢቆይም በአካባቢው በተሰራው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ እና በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር ውጤታማነት ዳግም ነፍስ ዘርቶ የአሳ ምርት እስከ መስጠት ደርሷል፡፡
በሃይቁ ዙሪያ የተለያዩ የባህል እቃ መሸጫዎች እንዲኖሩ በማድረግ ከቱሪዝም መስህቦች አንዱ እንዲሆን ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆኑንም አክለዋል፡፡
የጨርጨር ሃይቅ የሚገኝበት ሃብሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሐሰን መሐመድ ሃይቁ ለዘመናት ለአካባቢው ማህበረሰብ የመኖር ህልውና የነበረና በመሃል ደርቆ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
እንደ ሀረመያ እና ጨርጨር ጠፍተው የተመለሱ ሀይቆችንም ሆነ ያሉትን በአግባቡ አልምቶና አስተዋውቆ ከዘርፉ የቱሪዝም ገቢ ማመንጨት ማስቻል በክልሉ መንግስት ትኩረት ካገኙ ተግባራት መካከል መሆኑን ኢፕድ ዘግቧል ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv









