
አዲስ አበባ | መስከረም 15 2016| NBC ETHIOPIA- ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺህ 498ኛው «የመውሊድ» በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡
«መውሊድ» የነቢዩ መሐመድ የልደት ቀን ነው፡፡ በበርካታ ሀገራት የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የነቢዩ መሐመድን የልደት ቀን ምክንያት በማድረግ ለፈጣሪና ለነቢዩ ውዳሴ በማቅረብ፣ ቁርዓን በመቅራትና ስጦታዎችን በመለዋወጥ ያከብሩታል፡፡ በኢትዮጵያም የእምነቱ ተከታዮች ከተለያዩ ስለፈጣሪያቸውና ስለነቢዩ ሙሃመድ ጥልቅ ፍቅር ምስጋና በማድረስ፣ በጸሎትና በምህላ፣ ቁርዓን በመቅራትና ለሕዝቧ በፍቅርና በሰላም እንዲኖሩ በመጸለይና በመመረቅ የሚያከብሩት በዓል ነው ብለዋል፡፡
አክለውም የመውሊድ በዓልን ስናከበር እርስ በእርሳችን በመረዳዳትና በመደጋገፍ ከሁለንተናዊ ችግሮቻችን የምንሻገርበት መሆን አለበት፡፡ ከመጠላለፍና ከመገፋፋት ወጥተን መታሳሰብና መደጋገፍ ይኖርብናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ችግሮቻችንን ለመሻገር እና መጪውን ብሩህ ለማድረግ የምንችለው ዛሬም ነገም ስለችግሮቻችን በማውራት ሳይሆን በሁሉም መስክ በተሰማራንበት የተጣለብንን ኃላፊነት ስንወጣ ብቻ ነው፡፡
ሀገራችንን ከችግር፣ ከድኽነት፣ ካለመግባባት፣ ከመገፋፋት ትብታብ በማላቀቅ ትውልዱን ወደቀጣዩ የከፍታ ምዕራፍ ለማሻገር ለእውነት፣ ለፍትሕንና ለሕግ የበላይነት ተገዢ መሆን ይጠበቅብናል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv









