አዲስ አበባ | መስከረም 14 2016| NBC ETHIOPIA -ፍቅር ሰላም አንድነት የክብረ በዓላት በረከት በሚል መሪ ቃል የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዙሪያ ሲምፖዝየም ተካሄደ ።

መድርኩን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሲሆን የሀይማኖት አባቶችን ጨምሮ በርካታ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
በዝግጅቱ የመስቀል ደመራ በተመለከተ መነሻ ፅሁፍ ቀርቧል።መስቀል ከሀይመኖታዊ አስተምሮ በዘለለ በማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ የተመ ዘገበ በመሆኑ የሁሉም ህብርተብ ንብረት ስለሆነ የሁሉንም ጥበቃ ይፈልጋል የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል።
የአደባባይ ክብረ በዓል የሆነው መስቀል ደመራ የአብሮነትና አንድነት ማሳያ በመሆኑ ኢትዮጵዊያን አንድንትን የሚያጠናክሩበት መሆን ይኖርበታል የሚለው በመድረኩ ተንፀ ባርቋል።
ክብረ በዓሉ አስተምሮቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር በማድረግ ማህበራዊ መስተጋበር በማጠናከር መከበር ይገባል፤ ለዚህም ሁሉም ሀላፊነት አለበት የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡
በሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram- https://t.me/nbcethiopiatv