አዲስ አበባ | መስከረም 15 2016| NBC ETHIOPIA -የመስቀል ደመራ በዓል ከሃይመኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር ለሀገር አንድነት የሚያበረክተው ሚና ትልቅ በመሆኑ ሊጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ፍቅር፣ ሰላም፣ አንድነት- የክብረ በዓላት በረከት በሚል መሪ ቃል የመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዙሪያ በትናንትናው ዕለት ሲምፖዝየም አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው፤ መስቀል ደመራ ትርጉሙ ትልቅ ነው። በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ እምርታ የሚያስገኝ በመሆኑ ይህን ቅርስ ሃማኖታዊ እሴቱን እንደጠበቀ ከትውልድ ወደትውልድ እንዲተላለፍ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርሲቲያን ስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ዋና ኃላፊ መላከ ሰላም ቆሞስ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ (ዶክተር ) ስለ መስቀል ደመራ በዓል ጥናታዊ ጽሑፍ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የመስቀል ደመራ በዓል በአደባባይ በሚከበርበት ጊዜ ሃይማኖታዊ እሴቱ እንዳይደበዝዝ ቤተክርስቲያን በእጅጉ እየለፋችበት ትገኛለች።
በሲምፖዚየሙ ላይ የመስቀል ደመራ በዓል ከሃይማኖታዊ ዳራው አንጻር እንዴት ይቃኛል የሚል እና የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች አስፈላጊነት ምንድነው የሚሉ አውደ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












