አዲስ አበባ | መስከረም 14 2016| NBC ETHIOPIA-የመውሊድ በዓል አምላክን በመማጸንና እስላማዊ ስርዓትን በጠበቀ መልኩ ሊከበር እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልከሪም ሼህ በድረዲን እንደገለፁት፤1498ኛው የነብዩ መሀመድ መውሊድ በአል መስከረም 16 የሚከበር በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ የመውሊድ በአል ሲያከብር ያለውን በማካፈልና በመረዳዳት ሊሆን ይገባል፡፡
1498ኛው የነብዩ መሀመድ መውሊድ በአል “የይቅርታው ነብይ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሀ ግብሮች በአንዋር መስጂድ ይከበራል ያሉት ሼህ አብዱልከሪም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበር በዓል በመሆኑ ነቢያችን እንደሚሉን በመተሳሰብ እና በመተዛዘን እንዲሁም በመረዳዳት ማክበር ይኖርብናል ብለዋል፡፡
ነብዩ መሐመድ በእስልምና ሀይማኖት በነበራቸው አስተምህሮት የሰው ልጆች ያለ ዘርና ሃይማኖት ልዩነት የምድር ፍጡራን ሁሉ እኩል መሆናቸውን ሲያስተምሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡
በአሉን ልዩ ልዩ የግልና የቡድን ኢባዳዎችን (መልካም ሥራን) በመፈፀም የአገሪቱ ሰላም እንዲሟላ አስተማማኝ ደህንነት እንዲሰፍን ዱአ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቅሰው ህዝበ ሙስሊሙ በአሉን ሲያከብር የነብዩ መሀመድ ስነ ምግባርን በመላበስና ለሌሎች አርአያ በመሆን ሊያከብሩ ይገባል ማለታቸውን ኢ ፐ ድ ዘግቧል
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












