አዲስ አበባ | መስከረም 11 2016| NBC ETHIOPIA -በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማን የአረንጓዴ ሽፋን 30 በመቶ ለማድረስ አቅደን እየሠራን ነው ሲሉ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አዲስ አበባ ከተማ የአረንጓዴ ሽፋንን ቀደም ሲል ከነበረበት ሁለት ነጥብ ስምንት በመቶ በለውጡ ዘመን ወደ 15 በመቶ ማሳደግ ተችሏል፡፡ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታትም የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን 30 በመቶ ለማድረስ ዕቅድ ይዘን እየሠራን ነው፡፡
በአረንጓዴ አሻራ ባለፉት አምስት ዓመታት እንደ ሀገርና ከተማ የተመዘገበው ውጤት በትብብር ከተሠራ በሁሉም መስክ ስኬታማ መሆን እንደሚቻል ማሳያ ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ በአዲስ አበባ ከተማ በክረምት ወቅት 17 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ ከዕቅድ በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉን ገልጸዋል፡፡
እንደ ኢፕድ ዘገባ በከተማዋ በክረምት ወቅት በነበረው የችግኝ ተከላ መርሀግብርም የፍራፍሬ ችግኞችና ለከተማ ውበት የሚሆኑ የተለያዩ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












