
አዲስ አበባ | መስከረም 2 2015| NBC ETHIOPIA – በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የዘርፉ ምሁር ዶክተር ኃይለየሱስ ታዬ፤ የፌደራሊዝም ስርዓት የግልና የጋራ ፍላጎቶችና ጥቅሞችን ሚዛን ለማስጠበቅ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ።
ከጋራና ከግል ፍላጎቶች አንዱ ካጋደለ ችግር ስለሚሆን ሁለቱን አቻችሎ መሄድ እንደሚገባ ጠቅሰው በተለይም ፖለቲከኞችና ምሁራን የመሐል ሚናን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያን የፌደራል ስርዓት በጥሩ መሰረት ላይ በማኖር ለማስቀጠል ከታችኛው የአስተዳደር እርከን ጀምሮ በትኩረት መስራት ይገባልም ነው ያሉት።
ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መዋቅሩን ማጽናት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ይህም ጠንካራ አገረ መንግስት ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።
የብዝሃነት መገለጫ የሆነችው ኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ስርዓት አስፈላጊ በመሆኑ ብዝሃነትን በአግባቡ የሚያስተናግድ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
FACEBOOK-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት