አዲስ አበባ | መስከረም 3 2016| NBC ETHIOPIA-የአፍሪካ ልማት ባንክ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሃይል አቅርቦትን ለማሻሻል የሚያግዝ የ1 መቶ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ፈንድ ማጽደቁን አስታወቀ።

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ያጸደቀው የገንዘብ ድጋፍ 52 ሚሊዮን ዶላሩ ከአፍሪካ ልማት ፈንድ የተገኘ ነው ተብሏል።
ቀሪው የገንዘብ ድጋፍ ደግሞ የባንኩ የብድር አጋር ከሆነው በኮሪያ-አፍሪካ የኢነርጂ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ስምምነት ከኮሪያ የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ፈንድ የተገኘ ነው ተብሏል።
የባንኩ የኃይል ሥርዓት ልማት ዳይሬክተር ባቺ ባልዴህ ፕሮጀክቱ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ያለውን የኃይል ቋት አቅም በማሳደግ ታዳሽና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን የሚያሳድግ ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ 157 ኪሎ ሜትር እርዝማኔ ያለው የ400 ኪሎ ቮልት ባለ ሁለት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን እና ተያያዥ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን በሐረር፣ በጅግጅጋ እና በፋፈም የሚደረጉ ግንባታዎችን ያካተተ ነው።
ፕሮጀክቱ በቀጣይ ከሶማሊያ ጋር የኃይል ትስስር ለመፍጠር እንደ መነሻ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን ለአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ምጣኔ ኃብታዊ ውህደትን በማሳለጥና ንግድን በማቀላጠፍ ረገድ አስተዋፅኦ ያደርጋል ነው የተባለው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












