አዲስ አበባ | መስከረም 3 2016| NBC ETHIOPIA-በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ሰንሻይን በ የተገነባው ሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን የአረጋዊያን መንከባከቢያ ማዕከል እየተመረቀ ይገኛል።

ማዕከሉ ለ730 አረጋዊያን መጦሪያ፣ መጠለያና እንክብካቤ ለማድረግ የሚያችል አቅም እንዳለው በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ተገልፃል።
የአረጋዊያን መንከባከቢያ ማዕከሉ ከተማ አስተዳደሩ ከሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን ጋር ባደረጉት ስምምነት ግንባታው ተጠናቆ ለአረጋዊያን አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአረጋዊያን መንከባከቢያ ማዕከሉ መገንባቱ በጉብዝና እድሜቸው የተለያዩ አስተዋጽኦ ያደረጉ እና በእርጅና ዘመናቸው አጋዥ ያጡ አረጋዊያንን በመንከባከብ ደስተኛ እና የተረጋጋ ኑሮ እንኖሩ ለማስቻል ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
ማዕከሉ ለአረጋዊያን የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ክሊኒኮች እና ፋርማሲ፣ የምግብ ማብሰያና የመመገቢያ አዳራሽ፣ የመኝታ ቤት፣ ላውንደሪና የአረጋዊያን ንፅህና መጠበቂያ፣ የእደ ጥበብ መስሪያ እና የመዝናኛ ቦታዎችን አካቷል።
የአረጋዊያን መንከባከቢያ ማዕከሉ በ30 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን ከ600ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram – https://t.me/nbcethiopiatv












