አዲስ አበባ |ነሐሴ 30 2015| NBC ETHIOPIA-ዛሬ ማለዳ 1686 ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች እና የሃገር ባለውለታዎች እያስተላለፍን እንገኛለን:: ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በሁሉም ክፍለከተሞች በመተላለፍ ላይ የሚገኙት እነዚህ ቤቶች ደረጃችውን የጠበቁ እና መገልገያ እቃ የተሟላላቸው ሲሆን ለከፍተኛ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ አቅመደካማ ነዋሪዎች አዲሱን ዓመት በአዲስ ቤት በአዲስ ተስፋ በደስታ እንዲቀበሉ ያስችላቸዋል::
ይህ እንዲሳካ ከጎናቸው በመቆም ራዕያቸውን የተጋሩ ልበ-ቀና ባለሀብቶችን በከተማው ነዋሪ ስም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ምስጋና አቅርበዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc











