አዲስ አበባ |ነሐሴ 30 2015| NBC ETHIOPIA- የቲያትር ዘርፉ እንዲነቃቃ ያግዛል የተባለውን ስምምነት ናሽናል ሚዲያ አክሲዮን ማህበር (ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ) እና የኢትዮጵያ ቲያትር ባለሙያዎች ማህበር ተፈራረሙ፡፡

ዘርፉ በሚጠበቀው ልክ እንዳያድግ ካደረጉት ጉዳዮች መካከል የሚዲያው ለዘርፉ ሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑን የኢትዮጵያ ቲያትር ባለሙያዎች ማህበር አባላት በሰምምነት ፊርማው ወቅት ባደረጉት ውይይት ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም ዛሬ የተፈረመው የስምምነት ፊርማ ዘርፉን ለማነቃቃት ብሎም እንዲያድግ የሚኖረው አስተዋፅኦ የጎለ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ ዘርፉን ለማበረታታት ብሎም የኪነጥበብ አፍቃሪያን የቲያትር መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ ለማስቻል ነው ያለምንም ክፍያ ማስታወቂያዎችን ለማሰራጨት የተስማማው፡፡
የማህበሩ አባላትም ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ ጥበብን ለመደገፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አድንቀው ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/











