አዲስ አበባ |ነሐሴ 30 2015| NBC ETHIOPIA-የመከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ጄነራል ሩድዛኒ ማፕህዋንያ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሠረት ነው በሀገሪቱ የሥራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት።


ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በደቡብ አፍሪካ መከላከያ ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ በወታደራዊ ትርዒት የታጀበ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ለክብራቸውም 13 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።
ከደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት በሁለቱ ሀገራት እና ሕዝቦች መካከል ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረው ታሪካዊ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ለመጣው ወታደራዊ ትብብር ጠንካራ መሰረት የጣለ መሆኑን አንስተዋል።
በቀጣይ የትብብሮቹን አድማስ ለማስፋትና ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ማረጋገጣቸውን ኢ ፕ ድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc











