Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Uncategorized

መግለጫ፡ “ጳጉሜን ለኢትዮጵያ”

September 2, 2023
in Uncategorized
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ |ነሐሴ 27 2015| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር የአዲስ ዓመት መዳረሻ በሆኑት ስድስቱ የጳጉሜን ቀናት ከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውናቸውን መርሃ-ግብሮች አስመልክቶ ዛሬ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እናትአለም መለሰ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የጰጉሜን ቀናት ከፌዴራል መኔግስት ከወረዱ የጋራ እቅዶች ጋር በማጣጣም በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃም በደማቅ እና በተስፋ ሰጪ መርሃ-ግብሮች ይከናወኗል ብለዋል።

በዚሁ መሰረት ጳጉሜን አንድ የአገልጋይነት ቀን፣ ጳጉሜን ሁለት የመስዋዕትነት ቀን፣ ጳጉሜን ሦሰት የበጎነት ቀን፣ ጳጉሜን አራት የአምራችነት ቀን፣ ጳጉሜ አምስት የትውልድ ቀን እንዲሁም ጳጉሜ ስድስት የአምራችነት ቀን ሆነው በልዩ ልዩ መረሃ-ግብሮች እየተከበሩ ይውላል ብለዋል።

የቢሮ ኃላፊዋ በእያንዳንዱ የጲጉሜን ቀናት የሚተገበሩ  ዝርዝር መረሀ-ግብሮችን አስመልክተው እንደሰጡት ማብራሪያ መሰረት በጳጉሜን አንድ “የአገልጋይነት ቀን” ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ የህንጻ ምርቃት፣ በ33 ወረዳዎች የተገነቡ የስማርት አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ክፍት ማድረግ፣ ለአንጋፋ መምህራን ዕውቅና መስጠት፣ ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎትና ለጤና ባለሙያዎች በዕለቱ ዕውቅና እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በጳጉሜ ሁለት “የመስዋዕትነት ቀን” በሁሉም የመንግሥትና የግል ተቋማት ሰንደቅ-ዓላማ በመስቀል ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና የጸጥታ አካላትን ማመስገን፣ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ የፓናል ውይይት፣ በሁሉም ከፍለ ከተማና ወረዳ እንዲሁም ተቋማት የደም ልገሳ መርሃ-ግብር እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

ጳጉሜ ሦስት በሚውለው “የበጎነት ቀን” 860 ቤቶችን ለአቅመ -ደካሞች ማስተላለፍ፣ ለ3000 ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የማዕድ ማጋራት በከተማ ደረጃ ማከናወን፣ በሁሉም ክፍለ ከተማና ወረዳ የማዕድ ማጋራት ማድረግን ጨምሮ ቀጨኔ አካባቢ የተገነባው 20ኛው የተስፋ-ብርሃን የምገባ ምዕከል ምርቃት እንደሚከናወን የቢሮ ኃላፊዋ ይፋ አድርገዋል።

ጳጉሜ አራት በሚውለው “የአምራችነት ቀን” የሀገር ውስጥ ምርቶች ባዛርና ኤግዚቢሽን ፤የአያት የገበያ ማዕከል ምርቃት፣ አምራችነት የሚያበረታቱ ልዩ ልዩ መሰናዶዎችን በሚዲያ ተደራሽ ማድረግን የሚያካትት እንደሚሆን ተመላክቷል።

ጳጉሜ አምስት በሚውለው “የትውልድ ቀን” የመምህራን እና የወላጆች የውይይት መድረክ፣ አብሮነትን ለማጠናከር የሚረዳ የማስ እስፖርት፣ የወላጅ አልባ ህጻናት ርክክብ በማዘጋጀ ቤት መፈጸምን ጨምሮ ለትውልድ ሁለተናዊ ዕድገት ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን በሚዲያ ተደራሽ ማድረግን የሚያጠቃልል ይሆናል ብለዋል።

በተመሳሳይ ጳጉሜ ስድስት በሚውለው “የአብሮነት ቀን” በሁሉም ክፍለ ከተማና ወረዳ አብሮነትን ማዕከል ያደረጉ ውይይቶች፣ አብሮነትና ወንድማማችነትን የሚያጎሉ የሚዲያ ፕሮግራሞችን ጨምሮ የዋዜማ የመዝናኛ ሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚከናወን ወ/ሮ እናታለም መለሰ በመግለጫቸው ወቅት አስታውቀዋል።

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA                          

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook –https://nbcethiopia.com/news/

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

ከመቅደላ የተወሰደ ቅርስ ተመለሰ

Next Post

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት የተሰኘው የፓናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ-ርዕይ ተጀመረ

Related Posts

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ
News

ክሎፕ በጀርመን የመልሶ ግንባታ ወቅት ትዕግስት እንዲኖር ጠየቁ

November 13, 2026
17
የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Uncategorized

የመደመር መንግሥት: ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ

October 10, 2026
19
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል
News

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቀሌ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ጀምሮ ይጀምራል

October 9, 2026
16
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ
News

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ23 ሚኒስትሮች ሹመትን አጸደቀ

October 8, 2026
33
የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ
News

የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ሾሙ

October 2, 2026
23
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019
Uncategorized

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ ተገኝተው ያስተላለፉት መልዕክት | መስቀል 2019

September 27, 2026
23
Next Post

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ተምሳሌት የተሰኘው የፓናል ውይይትና የፎቶ ግራፍ አውደ-ርዕይ ተጀመረ

የዩክሬን መከላከያ ሚኒስትር ከሥልጣናቸው ተነሱ

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሮይ ኪን በአርሰናል ደጋፊዎች ድብደባ እንደተፈጸመበት ተዘግቧል

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?