አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26/2015፣ NBC ETHIOPIA- የግብርና ሚኒስቴር 2015/16 ምርትና ምርታማነትን በጥራትና በብዛት ለማምረት የተለያዩ መመሪያዎችን እና ደንቦችን በማጽደቅ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 3 ስትራቴጂክ መንገዶችን በመቅረጽ ማለትም ምግብና ስርአተ ምግብን ማስጠበቅ፤ ለውጭ ገበያ የሚሆን በቂ ምርት ማምርት እና ከውጭ የሚገቡትን በሃገር ውስጥ ምርት በመተካት ግብአት ማድረግን እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
በመኸር እርሻ 15 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ የሰብል ዘሮች መሸፈኑን የእርሻ እና የሆርቲካልቸር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መለስ መኮንን ተናገሩ።
ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ዘር ለመሸፈን መቻሉንም እና በመኸር እርሻው 3 ነጥብ 66 ሚሊየን ሄክታር የስንዴ ሰብል ለማረስ የታቀደ መሆኑም አንስተዋል።
በዚሁ ወቅት 1 ነጥብ 13 ሚሊየን ሄክታር የሩዝ ምርት ለማምረት በዕቅድ ተይዞ 990 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል፡፡ እስከ አሁን ባለው ሒደትም 1 ነጥብ 87 ሚሊየን ሄክታር መሬት ላይ ያለው ሰብል መሰብሰቡን ገልፀዋል።
በማህሌት ግርማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/