አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2015፣ NBC ETHIOPIA- መንግስት በአንዳንድ ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱትን አልባሳትን የሚከለክል ‘ግልጽ ህግጋቶችን’ ለትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች ለማስተላለፍ አቅዷል።

ፈረንሳይ በአንዳንድ ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱትን ረጅም ልብስ አባያ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለማገድ ማቀዷን የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስትር አስታወቋል።
ጋብሪኤል አታታል ለሚዲያ እንደተናገሩት መንግስት በጉዳዩ ላይ “ግልጽ ህጎችን” በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ የትምህርት ቤት ኃላፊዎች ለማስተላለፍ አስቧል። በተጨማሪም መላውን ሰውነት የሚሸፍነውን ልብስ ላይ የተጣለውን እገዳ ለማስፈጸም እንዲረዳቸው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ከትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች ጋር መነጋገር እንደሚፈልግ ተናግሯል።
በሀና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












