አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22/2015፣ NBC ETHIOPIA- የትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ከጉርድ ፎቶ ማስታወቂያ ሽያጭ ብቻ 7.1 ሚሊዯን ዶላር መሰብሰቡን ገለጸ::

ዶናልድ ትራምፕ ይህን ጉርድ ፎቶ የተነሱት በጆርጂያ ግዛት ክስ ከተመሰረተባቸው በኋላ እስር ቤት ውስጥ መሆኑ ታውቋል፡፡
በግዛቲቱ ሕግ መሰረት አንድ ተጠርጣሪ እስር ቤት ሲገባ አሻራውን ከሰጠ በኋላ የእስረኛ ጉርድ ፎቶ የግድ መነሳት ይኖርበታል።
ዶናልድ ትራምፕም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው እጅ ከሰጡ በኋላ አትላንታ ከተማ በሚገኝ እስር ቤት ቀርበው ጉርድ ፎቶ እንዲነሱ ተገደዋል።
እንደ አልጀዚራ ዘገባ ትራምፕ የምርጫ ውጤትን በሕገ ወጥ መንገድ ለመቀልበስ ሞክረዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው እንደነበርና የ 200 ሺህ ዶላር ዋስ በማስያዝ ከእስር ቤት መውጣታቸው የሚታወስ ነው።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












