አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2015፣ NBC ETHIOPIA – የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ጥያቄ በአጭር ጊዜ ተቀባይነት ማግኘቱ በዲፕሎማሲው መስክ እየተመዘገበ ላለው ስኬት ማሳያ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ብሩክ ሃይሉ ገለጹ።

ፕሮፌሰር ብሩክ እንደገለፁት ለረጅም ዓመታት ዓለም ከሁለትና ሶስት በማይበልጡ አገራት የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ስትመራ መቆየቷን ጠቅሰው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን አገራት ጥምረት እየፈጠሩ የበላይነቱን ተመጣጣኝ ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል አገር መሆኗ በሁሉም ዘርፍ መልካም እድል ይዞ የሚመጣ መሆኑን ፕሮፌሰር ብሩክ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ጥያቄ በአጭር ጊዜ ተቀባይነት ማግኘቱ በዲፕሎማሲው መስክ እየተመዘገበ ላለው ስኬት ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የብሪክስ አባል አገራት አጠቃላይ ገቢ 26 ትሪሊዮን ዶላር ሲሆን ይህም ከዓለም ምጣኔ ሃብት 26 በመቶውን የሚሸፍን መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት