አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2015፣ NBC ETHIOPIA – ወጣቶች ከየትኛውም የጥፋት እንቅስቃሴ በመራቅ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ቀናኢ ሆነው መስራት ይገባቸዋል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች ገለጹ።

በኢትዮጵያ የግጭትና ጦርነት አዙሪት አብቅቶ አገራዊ አንድነት፣ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የሃይማኖት አባቶቹ ጥሪ አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የስብከተ-ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ዋና ኃላፊ መላከ ሠላም ቆሞስ አባ ቃለ-ጽድቅ፤ ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ ዋነኛው ባለቤቶች ዜጎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ ሼህ ሁሴን በሽር በበኩላቸው፤ የሀገር ሰላም የማይመለከተው ዜጋ ስለሌለ ሁላችንም የሰላም ዘብ መሆን አለብን ሲሉም ገልጸዋል።
የሃይማኖት አባቶች ከግጭትና አለመረጋጋት ጉዳት እንጂ የሚገኝ አንዳችም ጥቅም ባለመኖሩ በተለይም ወጣቶች ይህንኑ ተገንዝበው ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ለህዝቦች አንድነት ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












