አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18/2015፣ NBC ETHIOPIA – በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን በአዲስ አባልነት ተቀብሏል።

ኢትዮጵያ ብሪክስን በአባልነት ለመቀላቀል በይፋ ጥያቄዋን ማቅረቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰኔ መገባደጃ 2015 ዓ.ም ላይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቁ እንድሚታወስ ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












